عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضيَ اللهُ عنهُما أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم:
نَهَى عَنْ كُلِّ ذِي نَابٍ مِنَ السِّبَاعِ، وَعَنْ كُلِّ ذِي مِخْلَبٍ مِنَ الطَّيْرِ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1934]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና:
ከሁሉም የክራንቻ ጥርስ ባለቤት አውሬና ከሁሉም ባለጥፍር በራሪ ስጋ (መብላትን) ከልክለዋል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1934]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የማንኛውንም በክራንቻ ጥርሶቹ አማካይነት የሚያድን አውሬና የማንኛውንም በጥፍሩ የሚቆርጥና የሚይዝ የሆነ በራሪ ስጋውን ከመብላት ከለከሉ።