عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ قَتَلَ مُعَاهَدًا لَمْ يَرَحْ رَائِحَةَ الْجَنَّةِ، وَإِنَّ رِيحَهَا تُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ أَرْبَعِينَ عَامًا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 3166]
المزيــد ...
ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡
"በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3166]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙዓሀድን በገደለ ሰው ላይ ያለበትን ከባድ ዛቻ ገለፁ። ሙዓሀድ ማለት ከከሀዲያን መካከል በቃል ኪዳንና በደህንነት ከለላ ወደ ኢስላም ሀገር የገባ ነው። እሱን የገደለ የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት ነው።