عن أنس رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«جَاهِدُوا المشركين بأموالكم وأنفسكم وألسنتكم».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وأحمد] - [سنن أبي داود: 2504]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አጋርያንን በገንዘባችሁ፣ በነፍሳችሁና በምላሳችሁ ታገሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 2504]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የአላህ ንግግር የበላይ እንድትሆን በተቻለ መጠን በሁሉም መንገድ ከሃዲያንን ለመታገልና እነርሱን ለመጋፈጥ በአቅም ልክ መታገልን አዘዙ። ከነዚህም መታገያዎች መካከል:
የመጀመሪያው: እነርሱን በመታገል ገንዘብ ማውጣት ነው። ይህም መሳሪያ በመግዛት፣ ለሙጃሂዶች ወጪ በማድረግና በመሳሰሉት ነው።
ሁለተኛው: ከሃዲያንን ለመፋለምና ለመከላከል በአካልና በነፍስ መውጣት ነው።
ሶስተኛው: ወደዚህ ሃይማኖት በምላስ በመጥራት፣ በነርሱ ላይ ማስረጃ በማቆም፣ ከነርሱ በማስጠንቀቅና በነርሱ ላይ በመመለስ ነው።