+ -

عن ابن عمر رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«كل مُسْكِرٍ خَمْرٌ، وكل مُسْكِرٍ حرام، ومن شرِب الخمر في الدنيا فمات وهو يُدْمِنُهَا لَمْ يَتُبْ، لَمْ يَشْرَبْهَا في الآخرة».

[صحيح] - [رواه مسلم وأخرج البخاري الجملة الأخيرة منه] - [صحيح مسلم: 2003]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2003]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይምሮን የሚያደነዝዝና የሚያስወግድ የሚጠጣም ይሁን የሚበላም ይሁን የሚሸተት ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ነገር ሁሉ ኸምርና አስካሪ መሆኑን ገለፁ። ሁሉም አስካሪና አይምሮን የሚያስወግድ ነገርም አነሰም በዛም አላህ ከልክሎታል። ከነዚህ የአስካሪ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አይነት የወሰደና በመውሰድ ላይም የዘወተረ እስኪሞት ድረስም ንስሀ ያልገባ ሰውም ጀነት ውስጥ መጠጣትን በመነፈግ የአላህ ቅጣት ይገባዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የኸምር ክልክልነት ምክንያቱ ማስከሩ ነው። ስለዚህ ማንኛውም አይነት አስካሪ ክልክል ነው።
  2. አላህ አስካሪ መጠጥን የከለከለው ትላልቅ ጉዳትና ብልሽቶችን ስለያዘ ነው።
  3. ኸምርን ጀነት ውስጥ ሲሆን መጠጣቱ የድሎትና የእርካታ ማሟያ ነው።
  4. በዚህ አለም አስካሪ መጠጥ ከመጠጣት ነፍሱን ያላቀበ አላህ ጀነት ውስጥ ከመጠጣት ይከለክለዋል። ምንዳ የሚሆነው በሰራው ስራ አይነት ነውና።
  5. ከሞት በፊት ከወንጀሎች ንስሀ በማድረግ ላይ መቻኮል እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።