عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضيَ اللهُ عنهُما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا أَسْكَرَ كَثِيرُهُ فَقَلِيلُهُ حَرَامٌ».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 3681]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደሏህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፡ «የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡
"ሲበዛ ያሰከረ ነገር ትንሹ ክልክል ነው።"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3681]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አብዝቶ ሲወሰድ አይምሮን የሚያስወግድ ማንኛውም የሚጠጣ ወይም የሚበላ ነገር ሁሉ አይምሮን የሚያስወግድበትን ያህል መጠን የማይደርስ ትንሽ እንኳ መውሰድ ክልክል መሆኑን ገለፁ።