عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
وُقِّتَ لَنَا فِي قَصِّ الشَّارِبِ، وَتَقْلِيمِ الْأَظْفَارِ، وَنَتْفِ الْإِبِطِ، وَحَلْقِ الْعَانَةِ، أَلَّا نَتْرُكَ أَكْثَرَ مِنْ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 258]
المزيــد ...
አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦
"ቀድሞ ቀመስን በመቀነስ፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብት ፀጉርን በመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር በመላጨት ዙሪያ ከአርባ ቀናት በላይ ሳናስወግድ እንዳንተወው የጊዜ ገደብ ተቀመጠልን።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 258]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወንድ ልጅ ቀድሞ ቀመሱን ለመቀነስ፣ የእጆችና እግሮችን ጥፍሮች ለማሳጠር፣ የብብትን ፀጉር ለመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅለውን ፀጉር ለመላጨት ከአርባ ቀናት በላይ ሳይቆረጥ እንዳይተው የጊዜ ገደብ አስቀመጡ።