+ -

عن أبِي هريرة رضي اللَّه عنه: سمعتُ النبِيّ صلى الله عليه وسلم يقول:
«الفِطْرَةُ خمسٌ: الخِتَانُ والاستحدادُ وقصُّ الشَّارِبِ وتقليمُ الأظفارِ وَنَتْفُ الآبَاطِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5891]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5891]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመልክተኞች ሱናዎችና ከኢስላማዊ መገለጫዎች አምስቱን አብራሩ፦
የመጀመሪያው፦ መገረዝ ነው። እሱም ከወንድ ልጅ ብልት ከክርክሩ ከፍ ብሎ ያለውን ጭማሪ ቆዳና ከሴት ልጅ ብልት ደግሞ ከወንድ ብልት መግቢያ ስፍራ ከፍ ብሎ ያለውን ቆዳ ከጫፉ ቀንሶ መቁረጥ ነው።
ሁለተኛው: የብልትን ፀጉር መቁረጥ ነው። ይህም ከብልት ዙሪያ ያለውን ፀጉር መላጨት ነው።
ሶስተኛው: ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር: እሱም በወንድ ልጅ የላይኛው ከንፈር ላይ የበቀለን ፂም ከንፈሩ በግልፅ እስኪታይ መቁረጥ ነው።
አራተኛው: ጥፍሮችን መቁረጥ ነው።
አምስተኛው: የብብትን ፀጉር መንጨት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ የሚወዳቸው፣ የሚቀበላቸውና ያዘዘባቸው የሆኑ የመልክተኞቹ ሱናዎች ወደ ምሉእነት፣ ንፅህናና ቁንጅና የሚጣሩ መሆናቸውን እንረዳለን።
  2. እነዚህን ነገሮች ተጠባብቆ መፈፀም የተደነገገ መሆኑንና ከነዚህ ጉዳዮች አለመዘናጋት እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. እነዚህን ጉዳዮች በአግባቡ መፈፀም ዲናዊና አለማዊ ጥቅሞች አሉት። ከነሱም ውስጥ፦ አካልን ማስዋብ፣ ሰውነትን ማፅዳት፣ ለንፅህና ጥንቁቅ መሆን፣ ከሀዲያንን መቃረንና የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ይገኝበታል።
  4. በሌላ ሐዲሥ ውስጥ ከነዚህ አምስት ተፈጥሯዊ ሱናዎች ውጪ ያሉ ተጨማሪ ሱናዎች፤ ለምሳሌ: ፂምን መልቀቅ (ማፋፋት)፣ ሲዋክና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።