عَنْ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْها أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ دَخَلَ عَلَيْهَا فَزِعًا يَقُولُ:
«لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَيْلٌ لِلْعَرَبِ مِنْ شَرٍّ قَدِ اقْتَرَبَ، فُتِحَ اليَوْمَ مِنْ رَدْمِ يَأْجُوجَ وَمَأْجُوجَ مِثْلُ هَذِهِ» وَحَلَّقَ بِإِصْبَعِهِ الإِبْهَامِ وَالَّتِي تَلِيهَا، قَالَتْ زَيْنَبُ بِنْتُ جَحْشٍ فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ: أَنَهْلِكُ وَفِينَا الصَّالِحُونَ؟ قَالَ: «نَعَمْ إِذَا كَثُرَ الخَبَثُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3346]
المزيــد ...
ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ እንዲህ አያሉ ደንግጠው ገቡ:
"ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።" አሉና በአውራ ጣታቸውና በጠቋሚ ጣታቸው ክብ አደረጉ። ዘይነብ ቢንት ጀሕሽም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በመካከላችን ደጋጎች እያሉ እንጠፋለን?" አለች። እርሳቸውም "አዎን ፀያፍ የበዛ ጊዜ" አሏት።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3346]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- ዘንድ ደንግጠውና ፈርተው አስከፊ ክስተት እንደሚከሰት ለማሳወቅ ላኢላሃ ኢለሏህ እያሉ ገቡ። ከዚህ አስከፊ ክስተት ወደ አላህ በመጠጋት ካልሆነ በቀር መዳን አይገኝምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: መከሰቱ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው፤ ዛሬ ዙልቀርነይን ገንብቶ ከዘጋው የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ ይህን ያህል ተከፍቷል። በአውራ ጣታቸውና በሚቀጥለው ጣታቸውም ክብ አድርገው አሳዩዋት። ዘይነብም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- "በመካከላችን ደጋጎችና አማኞች እያሉ እንዴት አላህ በኛ ላይ ጥፋትን ይሾምብናል?" አለች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሷ "እንደ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥና ሌሎች የአመፅና የወንጀል ፀያፍ ተግባራት የበዙ ጊዜ ጥፋት ሁሉንም ያዳርሳል።" አሏት።