عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَألَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا دَخَلَ الخَلاَءَ قَالَ: «اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الخُبُثِ وَالخَبَائِثِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 142]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 142]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሽንት ወይም ከሰገራ ለመፀዳዳት ወደ ስፍራው መግባት የፈለጉ ጊዜ ከወንድ ሰይጣኖችና ከሴት ሰይጣናት ክፋት በአላህ ይጠበቁና ወደርሱም ይጠጉ ነበር። በተጨማሪ "አልኹብሢ ወልኸባኢሥ" የሚለው ቃል ክፋትና ነጃሳ ተብሎም ተተርጉሟል።