+ -

عَنْ أَبِي أَيُّوبَ الأَنْصَارِيِّ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا أَتَيْتُمُ الغَائِطَ فَلاَ تَسْتَقْبِلُوا القِبْلَةَ، وَلاَ تَسْتَدْبِرُوهَا وَلَكِنْ شَرِّقُوا أَوْ غَرِّبُوا» قَالَ أَبُو أَيُّوبَ: فَقَدِمْنَا الشَّأْمَ فَوَجَدْنَا مَرَاحِيضَ بُنِيَتْ قِبَلَ القِبْلَةِ فَنَنْحَرِفُ، وَنَسْتَغْفِرُ اللَّهَ تَعَالَى.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 394]
المزيــد ...

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ" አቡ አዩብ እንዲህ አለ "ሻም ስንገባ ወደ ቂብላ አቅጣጫ የተገነባ መፀዳጃ ቤት አገኘን። ትንሽ ዘንበል እያልን እየተፀዳዳን አላህንም ምህረት እንጠይቀዋለን።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 394]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሽንትም ይሁን ለሰገራ መፀዳዳት የፈለገ ሰው ወደ ካዕባ አቅጣጫ ዞሮም ይሁን ለካዕባ ጀርባን ሰጥቶ መፀዳዳቱን ከለከሉ። ቂብላው እንደ መዲና ነዋሪዎች ከሆነ ማድረግ ያለበት ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ አቅጣጫ ዘንበል ማለት ነው። ቀጥሎ አቡ አዩብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ወደ ሻም የገቡ ጊዜ ወደ ካዕባ አቅጣጫ የተገነባ ለመፀዳጃነት የተዘጋጀ መፀዳጃ ቤት እንዳገኙ፤ በአካላቸውም ከቂብላ ዘንበል እንደሚሉና ከዚህም ጋር ግን አላህን ምህረት እንደሚጠይቁ ተናገረ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በዚህ ድንጋጌ የተፈለገው ጥበብ የላቀውን ካዕባ ማላቅና ማክበር ነው።
  2. ከመፀዳጃ ስፍራ ከወጣን በኋላ ኢስቲግፋር ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የማስተማር ዘዴ ማማሩን እንረዳለን። ይህም ክልክሉን ከጠቀሱ በኋላ የሚፈቀደውን በመጠቆማቸው ነው።
ተጨማሪ