عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: إِنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«إِذَا شَرِبَ الْكَلْبُ فِي إِنَاءِ أَحَدِكُمْ فَلْيَغْسِلْهُ سَبْعًا».
ولمسلم: « أولاهُنَّ بالتُراب».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 172]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 172]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውሻ እቃ ውስጥ ምላሱን ያስገባ ጊዜ እቃው ሰባት ጊዜ እንዲታጠብ አዘዙ። ከነዚህ ሰባት ትጥበቶች የመጀመሪያውን በአፈር ቀላቅሎ ይጠበው ይህም ከዛ በኋላ ውሃ በተደጋጋሚ እንዲፈስበት ነው። በዚህም ከነጃሳውና ከጉዳቶቹ የተሟላ መፅዳት ይገኛል።