+ -

عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُكْثِرُ أَنْ يَقُولَ: «يَا مُقَلِّبَ القُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ»، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ، آمَنَّا بِكَ وَبِمَا جِئْتَ بِهِ فَهَلْ تَخَافُ عَلَيْنَا؟ قَالَ: «نَعَمْ، إِنَّ القُلُوبَ بَيْنَ أُصْبُعَيْنِ مِنْ أَصَابِعِ اللهِ يُقَلِّبُهَا كَيْفَ يَشَاءُ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 2140]
المزيــد ...

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶና ይዘውት በመጡት ሃይማኖት አምነናል። በኛ ላይ የሚፈሩልን ጉዳይ አለ ማለት ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "አዎን ልቦች በአላህ ሁለት ጣቶች መካከል ናቸው። እንደፈለገው ይገለባብጣታል።" አሉኝ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2140]

ትንታኔ

አብዛኛው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓ በኢስላምና በአምልኮ ላይ መፅናትንና ከጥመት መራቅን አላህን የሚጠይቁበት ነበር። አነስ ቢን ማሊክም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህን ዱዓ በማብዛታቸው ተደነቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልቦች ከአላህ ጣቶች መካከል በሁለቱ ጣቶች መሀል እንደሆኑና እንደፈለገም እንደሚያገለባብጣቸው ነገሩት። ቀልብ የኢማንና ክህደት መኖሪያ ናት። ቀልብ ቀልብ ተብሎ የተሰየመው በብዛት ስለሚገለባበጥ ነው። ቀልብ ድስት በሚንተከተክ ጊዜ ከሚገለባበጠው በላይ ይገለባበጣል። አላህ ለሻለት ሰው ቀልቡን በቀናው መንገድ ላይና በኢስላም ላይ ያፀናለታል። አላህ ጥመት የሻለትን ሰው ደግሞ ቀልቡን ከቀናው መንገድ ወደ ጥመት ያዞርበታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الصربية الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጌታቸው ያላቸው መዋደቅና መተናነስን እንዲሁም ኡመታቸውም ይህንን ጥያቄ እንዲጠይቁ መጠቆማቸውን እንረዳለን።
  2. በኢስላም ላይ የመፅናትና ቀጥ የማለት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን። ዋናው ቦታ የሚሰጠውም ፍፃሜያችን ነው።
  3. አንድ ባሪያ በኢስላም ላይ መፅናትን ከአላህ ከመፈለግ ለአይን ጨረፍታ ያህል እንኳ አይብቃቃም።
  4. ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተከትለን ይህንን ዱዓ በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  5. በእስልምና ላይ መፅናት አንድ ባሪያ ሊለፋለት የሚገባና በርሱም ጌታውን ሊያመሰግንበት የሚገባ ትልቁ ፀጋ ነው።