عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«بَادِرُوا بِالْأَعْمَالِ فِتَنًا كَقِطَعِ اللَّيْلِ الْمُظْلِمِ، يُصْبِحُ الرَّجُلُ مُؤْمِنًا وَيُمْسِي كَافِرًا، أَوْ يُمْسِي مُؤْمِنًا وَيُصْبِحُ كَافِرًا، يَبِيعُ دِينَهُ بِعَرَضٍ مِنَ الدُّنْيَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 118]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 118]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልካም ስራ ከመፈፀም የሚከለክሉና የሚያቅቡ ፈተናና ማምታቻዎች መጥተው መልካም ስራ መስራት ከባድ ከመሆኑ በፊት አማኞች ወደ መልካም ስራ እንዲቻኮሉና እንዲያበዙ አነሳሱ። ይህም ፈተና እንደ ሌሊት ቁራጭ ድቅድቅ ጨለማ በመሆኑ እውነቱ ከሀሰት ጋር ተደበላልቆ ለሰዎች እውነትን ከውሸት መለየት የሚከብድበት ፈተና ነው። ከፈተናዋ መክበድ የተነሳ ሰውዬው አማኝ ሆኖ አንግቶ ከሀዲ ሆኖ እስኪያመሽ፤ አማኝ ሆኖ አምሽቶ ከሀዲ ሆኖ እስኪያነጋና ጠፊ በሆነው አለማዊ ጥቅም ሃይማኖቱን እስኪተው ድረስ ሰዎች ይዋልላሉ።