عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«السَّاعِي عَلَى الأَرْمَلَةِ وَالمِسْكِينِ، كَالْمُجَاهِدِ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، أَوِ القَائِمِ اللَّيْلَ الصَّائِمِ النَّهَارَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5661]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5661]
ባሏ ለሞተባትና የሚያስፈልጋትን ጉዳይ የሚያሟላላት አንድም ሰው ለሌላት ሴት እና ተረጂ ለሆነ ሚስኪን ጥቅማቸውን በሟሟላት የቆመ እንዲሁም አላህ ዘንድ ምንዳን በማሰብ ለነርሱ ወጪ የሚያደርግ ሰው በምንዳ ደረጃ ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ወይም ለተሀጁድ ሶላት ሳይደክም እየቆመ ምንም ሳያፈጥር እንደሚፆም ሰው አምሳያ መሆኑን ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ።