عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمِنين رَضيَ اللهُ عنها قَالَتْ:
جَاءَتْنِي مِسْكِينَةٌ تَحْمِلُ ابْنَتَيْنِ لَهَا، فَأَطْعَمْتُهَا ثَلَاثَ تَمَرَاتٍ، فَأَعْطَتْ كُلَّ وَاحِدَةٍ مِنْهُمَا تَمْرَةً، وَرَفَعَتْ إِلَى فِيهَا تَمْرَةً لِتَأْكُلَهَا، فَاسْتَطْعَمَتْهَا ابْنَتَاهَا، فَشَقَّتِ التَّمْرَةَ الَّتِي كَانَتْ تُرِيدُ أَنْ تَأْكُلَهَا بَيْنَهُمَا، فَأَعْجَبَنِي شَأْنُهَا، فَذَكَرْتُ الَّذِي صَنَعَتْ لِرَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: «إِنَّ اللهَ قَدْ أَوْجَبَ لَهَا بِهَا الْجَنَّةَ، أَوْ أَعْتَقَهَا بِهَا مِنَ النَّارِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2630]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«አንዲት ሚስኪን ሴትዮ ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ እኔ ዘንድ መጣች። ሶስት ቴምሮችን ሰጠኃት። ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሰጠቻቸው። የቀረችውንም ተምር ራሷ ልትበላው ወደ አፏ ስታነሳ ሁለቱ ልጆቿም ጎመጁ ልትበላው ፈልጋ የነበረችውንም ተምር ለሁለት ሰነጠቀችና አካፈለቻቸው። ስራዋ እጅግ አስደንቆኝ ያደረገችውን ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁላቸው። እርሳቸውም "አላህ ለርሷ በዚህ ስራዋ ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም በዚህ ስራዋ ከእሳት ነፃ አውጥቷታል።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2630]
የአማኞች እናት ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዳወሳችው: አንድ ሚስኪን ሴት ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ ዓኢሻን ለመነቻት። ዓኢሻም ሶስት ቴምሮችን ሰጠቻት። ለእያንዳንዷ ልጆቿ አንድ አንድ ቴምር ሰጠችና አንዷን ቴምር ደግሞ ልትበላት ወደ አፏ አስጠጋች። ነገር ግን ልትበላት የፈለገቻትን አንዷን ቴምር ሁለቱ ልጆቿ መፈለጋቸውን ተረዳችና ያንኑም ቴምር ለሁለት ከፍላ አከፋፈለቻቸው። የሴትዬዋ ጉዳይም ዓኢሻን (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ስለደነቃት ሴትዬዋ የሰራችውን ሁሉ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "አላህ በዚህች ተምር ምክንያት ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም ደሞ በዚህች ተምር ምክንያት ከእሳት ነፃ አድርጓታል።