+ -

عَنْ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّمَا مَثَلُ الْجَلِيسِ الصَّالِحِ وَالْجَلِيسِ السَّوْءِ كَحَامِلِ الْمِسْكِ وَنَافِخِ الْكِيرِ، فَحَامِلُ الْمِسْكِ: إِمَّا أَنْ يُحْذِيَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَبْتَاعَ مِنْهُ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ مِنْهُ رِيحًا طَيِّبَةً، وَنَافِخُ الْكِيرِ: إِمَّا أَنْ يُحْرِقَ ثِيَابَكَ، وَإِمَّا أَنْ تَجِدَ رِيحًا خَبِيثَةً».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2628]
المزيــد ...

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2628]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎችን በምሳሌ ገለፁ።
የመጀመሪያው አይነት: ወደ አላህ የሚጠቁም፣ ወደ አላህ ውዴታ የሚመራና በአምልኮ ላይ የሚያግዝ መልካም ጓደኛ ነው። የርሱም ምሳሌ ሽቶ እንደሚሸጥ ሰው ምሳሌ ነው። ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይም ከርሱ መልካም መአዛን ታሸታለህ።
ሁለተኛው አይነት ደግሞ ከአላህ መንገድ የሚያቅብ፣ ወንጀል በመፈፀም ላይ የሚያግዝ ፣ መጥፎ ተግባራትን የምታይበት መጥፎ ጓደኛ ነው። የሱን አይነት ሰው ወዳጅና ጓደኛ አድርገህ በመያዝህም የሚያስወቅስህ ነው። የርሱም ምሳሌ ወናፍ እንደሚያናፋ ብረት ቀጥቃጭ ነው። እርሱም ወይ በሚፈነጣጠረው እሳት ልብስህን ያቃጥላል ወይም ወደርሱ በመቅረብህ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አዳማጩ ሀሳቡ እንዲገባው ምሳሌ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  2. የመልካምና የበጎ ባለቤቶችን በመቀማመጥ ላይና የብክለትና የመጥፎ ስነ ምግባር ባለቤቶችን በመራቅ ላይ መነሳሳቱና መበረታታቱን እንረዳለን።