عن أبي هريرة رضي الله عنه أَن النبيَّ صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم قَالَ:
«الرَّجُلُ عَلَى دِينِ خَلِيلِهِ، فَلْيَنْظُر أَحَدُكُم مَنْ يُخَالِل».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 4833]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4833]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰው ልጅ ፍፁም ጓደኛውንና ባልደረባውን በልማዱና ኑሮው እንደሚመሳሰል፤ ጓደኝነትም በስነምግባር፣ በባህሪና የኑሮ ዘይቤ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ገለፁ። ለዚህም ጓደኛ አመራረጣችንን እንድናሳምር ጠቆሙ። ምክንያቱም ጥሩ ጓደኛ ወደ ኢማን፣ ቅናቻና መልካም ነገር ይጠቁማል። ለባልደረባውም አጋዥ ይሆናልና።