+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَلاَ أُحَدِّثُكُمْ حَدِيثًا عَنِ الدَّجَّالِ، مَا حَدَّثَ بِهِ نَبِيٌّ قَوْمَهُ؟ إِنَّهُ أَعْوَرُ، وَإِنَّهُ يَجِيءُ مَعَهُ بِمِثَالِ الجَنَّةِ وَالنَّارِ، فَالَّتِي يَقُولُ إِنَّهَا الجَنَّةُ هِيَ النَّارُ، وَإِنِّي أُنْذِرُكُمْ كَمَا أَنْذَرَ بِهِ نُوحٌ قَوْمَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3338]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል። እርሷ ጀነት ናት የሚላት እሳት ናት። እኔ ኑሕም ህዝቦቹን እንዳስጠነቀቀው አስጠነቅቃችኋለሁ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3338]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረቦቻቸው ስለደጃል፣ ስለባህሪያቱና ምልክቶቹ ከርሳቸው በፊት ማንም ነቢይ ያልተናገረውን ነገሯቸው። ከዚህም መካከል:-
እርሱ አንድ‐ዓይና ነው።
አላህ ከርሱ ጋር ለዓይን በሚታይ መልኩ ጀነትና እሳት የሚመስልን ነገር እንዳደረገለት፤
ነገር ግን ጀነት መስሎ የሚታየው እሳት፣ እሳት መስሎ የሚታየው ጀነት ነው። እርሱን የታዘዘን ለሰው "ጀነት" መስሎ በሚታየው ውስጥ ይከተዋል። ነገር ግን እርሷ የምታቃጥል እሳት ናት። እርሱን ያመፀን ለሰው "እሳት" መስሎ በሚታየው ውስጥ ይከተዋል። ነገር ግን እርሷ ምርጥ ጀነት ናት። ቀጥለውም ልክ ኑሕ ለህዝቦቹ እንዳስጠነቀቀው ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከደጃል ፈተና አስጠነቀቁን።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የደጃል ፈተና ትልቅነትን እንረዳለን።
  2. ከደጃል ፈተና መዳን በእውነተኛ ኢማን፣ ወደ አላህ በመጠጋት፣ በመጨረሻው ተሸሁድ ወቅት ከርሱ በአላህ በመጠበቅና ከሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን በመሸምደድ ይገኛል።
  3. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው በፊት ያለ ማንም ነቢይ ያላብራራውን የደጃል ባህሪያት ለሙስሊሞች ማብራራታቸው ለኡመታቸው መመራት ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት ያስረዳናል።