+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أَسْرِعُوا بِالْجِنَازَةِ، فَإِنْ تَكُ صَالِحَةً فَخَيْرٌ تُقَدِّمُونَهَا، وَإِنْ يَكُ سِوَى ذَلِكَ، فَشَرٌّ تَضَعُونَهُ عَنْ رِقَابِكُمْ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1315]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ጀናዛን ፈጠን ብላችሁ ቅበሩ። ጀናዛው መልካም ከሆነ ወደ መልካም ነገር ማስቀደም ነው። ከዛ ውጪ ከሆነ ደግሞ መጥፎ ነገር ነው ከትከሻችሁ ማላቀቅ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1315]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀናዛን ለቀብር ማሰናዳት፣ ጀናዛው ላይ መስገድና መቅበር በፍጥነት እንዲከናወን አዘዙ። ጀናዛው መልካም ከሆነ ወደ መልካሙ የቀብር ፀጋ እያስቀደማችሁት ነው፤ ከዛ ውጪ ከሆነ ደግሞ መጥፎን ነገር ከትከሻችሁ እየተላቀቃችሁ ነው አሉ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ጀናዛን ለመቅበር መፍጠን ይወደዳል። ነገር ግን ሟቹ ላይ የከፋ ነገር ይደርሳል ተብሎ በሚያስፈራ መልኩ ወይም ተሸካሚዎቹና ሸኚዎቹ ላይ ችግር በሚያደርስ ልክ በተጋነነ መልኩ መሆን የለበትም።"
  2. ቀብርን ማፍጠን የሚቻለው ራስን መሳት ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚያሰጋ ድንገተኛ ሞት እስካልሆነ ድረስ ነው። ሞቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ወይም ቀብሩን ጥቂት ወቅት በማዘግየት እንደሰጋጆች መብዛት ወይም የቅርብ ዘመዶቹ መገኘት የመሰሉ ጥቅም የሚገኙበት ከሆነና በሟቹ ላይ ጉዳት ካልተፈራ በፍጥነት አለመቅበሩ ተገቢ ይሆናል።
  3. ሟቹ እድለኛ ከሆነ ለሟቹ ጥቅም ሲባል፤ ሟቹ እድለቢስ ከሆነ ደግሞ ለቀብሩ ሸኚዎች ጥቅም ሲባል በፍጥነት በመቅበር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ መልካም ካልሆኑ የጥመት ሰዎች ጋር ጓደኝነትን መተው እንደሚገባ እንረዳለን።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ