عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بن مسعودٍ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ مِنْ شِرَارِ النَّاسِ مَنْ تُدْرِكُهُ السَّاعَةُ وَهُمْ أَحْيَاءٌ، وَمَنْ يَتَّخِذُ الْقُبُورَ مَسَاجِدَ».
[حسن] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 3844]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›"
[ሐሰን ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 3844]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ መጥፎ ሰዎች ተናገሩ። እነርሱም በህይወት ሳሉ ሰአቲቱ (ቂያማ) የምትቆምባቸውና እነዚያ መቃብሮችን መስገጃ አድርገው በመያዝ እርሱ ዘንድና ወደርሱ በመዞር የሚሰግዱት ናቸው።