عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَدْخُلُ الْخَلَاءَ، فَأَحْمِلُ أَنَا وَغُلَامٌ نَحْوِي إِدَاوَةً مِنْ مَاءٍ وَعَنَزَةً فَيَسْتَنْجِي بِالْمَاءِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 271]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም እስቲንጃእ ያደርጉበት ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 271]
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እርሱና የርሱ እኩያ የሆነ ሌላ አገልጋይ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ መፀዳጃ ቤት በሚሄዱበት ወቅት ይከተሏቸው እንደነበረና ከራሳቸው ጋርም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲፀዳዱ እርሱ ላይ አንድ ነገር አንጠልጥለው የሚከልሉበት ወይም ለሶላታቸው መከለያ የሚያደርጉት እንደጦር ጫፍ አምሳያ ጫፉ ላይ ሹልነት ያለውን ዘንግ እንደሚሸከሙ፤ በተጨማሪም ከቆዳ በተሰራ ትንሽዬ የውሃ መያዣ ውሃ ሞልተው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደሚወስዱ ተናገረ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተፀዳድተው ሲጨርሱም ከሁለቱ አንዱ ውሃን ያቀብላቸውና በውሃው ኢስቲንጃእ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።