+ -

عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا يُمْسِكَنَّ أَحَدُكُمْ ذَكَرَهُ بِيَمِينِهِ وَهُوَ يَبُولُ، وَلَا يَتَمَسَّحْ مِنَ الْخَلَاءِ بِيَمِينِهِ، وَلَا يَتَنَفَّسْ فِي الْإِنَاءِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 267]
المزيــد ...

ከአቡ ቀታዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 267]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳንድ ስርዓቶችን አብራሩ። ወንድ ልጅ በሚሸናበት ወቅት ብልቱን በቀኝ እጁ መያዙን ከለከሉ፤ ከፊት ለፊት ብልትም ይሁን ከኋላ ብልት የሚወጣን ነጃሳ በቀኝ እጅ ማስወገዱንም ከለከሉ፤ ምክንያቱም ቀኝ እጅ የተዘጋጀችው የተከበሩ ድርጊቶችን ለመፈፀም ነውና። ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው የሚጠጣበት እቃ ውስጥ መተንፈሱንም ከልክለዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በስነ-ስርዓት እና በንፅህና እስልምና ቀዳሚ መሆኑን መገለፁ።
  2. ቆሻሻ ነገሮችን መራቅ እንደሚገባና የግድ መንካት ካለበትም በግራ መሆን እንዳለበት እንረዳለን።
  3. የቀኝ እጅ ደረጃና ከግራ እጅ በላጭ መሆኑን መገለፁ።
  4. እስላማዊ ድንጋጌ ምሉዕና አስተምህሮቶቹ ሁሉን አቀፍ መሆናቸውን እንረዳለን።