عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
إِنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَهَى أَنْ يُسْتَنْجَى بِرَوْثٍ أَوْ عَظْمٍ، وَقَالَ: «إِنَّهُمَا لَا تُطَهِّرَانِ».
[صحيح] - [رواه الدارقطني] - [سنن الدارقطني: 152]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ። "ሁለቱም አያፀዱም።" ብለዋል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።] - [ሱነን ዳረቁጥኒይ - 152]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሸና ወይም ሰገራውን ከተጠቀመ በኋላ በእንስሶች አጥንት ወይም በፍጋቸውና በፋንዲያቸው ከማደራረቅ ከለከሉ። እንዲህም አሉ: እርሷ ነጃሳን አታስወግድምም አታፀዳምም።