عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ إِذَا خَرَجَ مِنَ الغَائِطِ قَالَ: «غُفْرَانَكَ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 30]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 30]

ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት ተፀዳድተው ሲወጡ አላህ ሆይ ምህረትህን እጠይቃለሁ ይሉ ነበር።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. ከመፀዳጃ ስፍራ ሲወጣ "ጉፍራነክ" ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታቸው ጌታቸውን ምህረት እንደሚጠይቁ እንረዳለን።
  3. ከመፀዳጃ ቤት ሲወጣ ምህረትን የሚጠየቅበት ምክንያት አላህን ለብዙ ፀጋዎቹ ከማመስገን ስላጓደልን ሲሆን ከነዛም ፀጋዎቹ መካከል የሚያውከንን ነገር እንዲወጣ ማቅለሉ አንዱ ነው። በምፀዳዳበት ወቅት አንተን ከማውሳት ስለተጠመድኩ ምህረትህን እጠይቅሃለሁ ይባላልም ብለዋል።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (51)
ተጨማሪ