عَنْ عَمْرِو بْنُ سُلَيْمٍ الأَنْصَارِيُّ قَالَ: أَشْهَدُ عَلَى أَبِي سَعِيدٍ قَالَ: أَشْهَدُ عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الغُسْلُ يَوْمَ الجُمُعَةِ وَاجِبٌ عَلَى كُلِّ مُحْتَلِمٍ، وَأَنْ يَسْتَنَّ، وَأَنْ يَمَسَّ طِيبًا إِنْ وَجَدَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 880]
المزيــد ...
ከዐምር ቢን ሱለይም አልአንሷሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "አቡ ሰዒድ እንዲህ እንዳለ እመሰክራለሁ: 'የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ እንዳሉ እመሰክራለሁ:
"ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 880]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሙስሊሞች መካከል ጁሙዓ ሊሰግድ ግዴታ የሆነበት የደረሰ ወንድ ልጅ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠቡ ልክ እንደ ግዴታ አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገለፁ። በመፋቂያና በመሳሰሉት ጥርሱን ማፅዳቱም፤ እንዲሁም ማንኛውም መልካም መዓዛ ያለውን ሽቶ መቀባቱንም አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገለፁ።