+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَشَدَّ حَيَاءً مِنَ العَذْرَاءِ فِي خِدْرِهَا، فَإِذَا رَأَى شَيْئًا يَكْرَهُهُ عَرَفْنَاهُ فِي وَجْهِهِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6102]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል:
«ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6102]

ትንታኔ

አቡሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሳታገባና ወንዶች ጋር ሳትኗኗር በቤቷ ተሸሽጋ ከምትኖር ልጃገረድ ሴት የበለጠ አይነአፋር እንደነበሩ ተናገረ። እጅግ አይነአፋር ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ነገር የጠሉ ጊዜ ፊታቸው ይለዋወጣል እንጂ አይናገሩም። ይልቁኑም ባልደረቦቻቸው ፊታቸውን በመመልከት ያንን ነገር መጥላታቸውን ይረዳሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተላበሱት አይነአፋርነት መገለፁ። ይህ ባህሪም ትልቅ ስነምግባር ነው።
  2. የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይነአፋርነት የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ነው። የአላህ ክልከላ ከተደፈረ ግን ይቆጡ፣ ባልደረቦቻቸውንም የሚያዙና የሚከለክሉ ነበሩ።
  3. የአይነአፋርነትን ባህሪ በመላበስ መነሳሳቱን እንረዳለን። አይነአፋርነት ነፍስ መልካም ተግባር እንድትሰራና ፀያፍን እንድትተው ይገፋፋታልና።