عَنِ ابْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«سَتَكُونُ أَثَرَةٌ وَأُمُورٌ تُنْكِرُونَهَا» قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ فَمَا تَأْمُرُنَا؟ قَالَ: «تُؤَدُّونَ الحَقَّ الَّذِي عَلَيْكُمْ، وَتَسْأَلُونَ اللَّهَ الَّذِي لَكُمْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3603]
المزيــد ...
ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3603]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙስሊሞችን ገንዘብና ሌሎችንም አለማዊ ጉዳዮች በማዳላት ሙስሊሞችን በርሱ ላይ ካላቸው መብት በመከልከል እንደፈለጉ የሚያወጡ መሪዎች በሙስሊሞች ላይ እንደሚሾሙ ተናገሩ። በነርሱ ላይም የሚወገዙ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች እንደሚኖራቸው ተናገሩ። ሶሐቦችም (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በዚህ ሁኔታ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በገንዘብ ጉዳይ ብቻቸውን መጠቀማቸው በናንተ ላይ ለነርሱ ልታሟሉ ግዴታ የሆነባችሁን ከመስማትና ከመታዘዝ እንዳይገታችሁ። ይልቁንም ታግሳችሁ መስማትና መታዘዝ ላይ አደራችሁን። በትእዛዞቻቸውም አትቃረኗቸው (አትከራከሯቸው)። እንዲያስተካክላቸው፣ ክፋታቸውንና ግፋቸውን እንዲከላከልላችሁ ለናንተ ያላችሁንም ሐቅ ከአላህ ጠይቁ!