عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ عُمرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُما أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«كُلُّكُمْ رَاعٍ فَمَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، فَالأَمِيرُ الَّذِي عَلَى النَّاسِ رَاعٍ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْهُمْ، وَالرَّجُلُ رَاعٍ عَلَى أَهْلِ بَيْتِهِ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْهُمْ، وَالمَرْأَةُ رَاعِيَةٌ عَلَى بَيْتِ بَعْلِهَا وَوَلَدِهِ وَهِيَ مَسْئُولَةٌ عَنْهُمْ، وَالعَبْدُ رَاعٍ عَلَى مَالِ سَيِّدِهِ وَهُوَ مَسْئُولٌ عَنْهُ، أَلاَ فَكُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْئُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ። በሰዎች ላይ የተሾመ መሪ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ወንድ በቤተሰቡ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ሴት ልጅ በቧሏ ቤትና በልጆቹ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ናት። ስለነርሱም ትጠየቃለች። ባሪያ በአለቃው ገንዘብ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለርሱም ይጠየቃል። አዋጅ! ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኝ ሁሉም ሙስሊም ላይ የሚሸከመውና የሚጠብቀው ኃላፊነት እንዳለበት ተናገሩ። ኢማምና መሪ አላህ ባስጠበቃቸው ኃላፊነት እረኞች (ኃላፊዎች) ናቸው። በርሱ ላይም ሸሪዓቸውን መጠበቅ፣ በነርሱ ላይ ግፈኛ ከሆነ መጠበቅ፣ ጠላቶቻቸውን መታገልና ሐቃቸውን አለማጥፋት ይገባዋል። ወንድም ለቤተሰቡ ቀለብ በማሟላት፣ መልካም አኗኗር በማኖር፣ በማስተማርና ስርዓት በማስያዝ ላይ ኃላፊነት አለበት። ሴትም በባሏ ቤት ውስጥ ቤቱን ባማረ መልኩ በማስተናበርና ልጆቹን በማነፅ ላይ ኃላፊነት አለባት። ስለዚህም ትጠየቃለች። አገልጋይ ባሪያና ተቀጣሪም በአለቃው ገንዘብ ላይ በእጁ ያለውን የአለቃውን ገንዘብ በመጠበቅ፣ እርሱን በማገልገል ሀላፊ ነው። ስለዚህም ይጠየቃል። እያንዳንዱ ሰው አላህ በሰጠው ሀላፊነት ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። እያንዳንዱም ሰው ስለ ሀላፊነቱ ይጠየቃል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአጠቃላይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተጠያቂነት ያለ ሲሆን ሁሉም በልኩ፣ በችሎታውና በሀላፊነቱ ልክ ተጠያቂ ው።
  2. የሴት ኃላፊነት ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። ይህም በባሏ ቤት እና በልጆቿ ላይ ያላትን ግዴታዎች መወጣት ስለሆነ ነው።