عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«أَكْمَلُ الْمُؤْمِنِينَ إِيمَانًا أَحْسَنُهُمْ خُلُقًا، وَخَيْرُكُمْ خَيْرُكُمْ لِنِسَائِهِمْ».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 1162]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፡
'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1162]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች መካከል ኢማኑ የሞላው ስነምግባሩ ያማረ ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለሰዎች ፊቱን ፈታ በማድረግ፣ መልካምን በመስጠት፣ ንግግርን በማሳመርና ሰዎችን ከማወክ በመቆጠብ ነው።
ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ለምሳሌ ለሚስቱ፣ ለሴት ልጆቹ፣ ለእህቶቹና ለቅርብ ዘመዶቹ ምርጥ የሆኑ ናቸው። ምክንያቱም ሴቶች በመልካም ስነምግባር ሊኗኗራቸው ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የተገቡ ስለሆኑ ነው።