عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنهما أنَّ رَسولَ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ عليْه وسلَّمَ، قال:
«قَدْ أَفْلَحَ مَن أَسْلَمَ، وَرُزِقَ كَفَافًا، وَقَنَّعَهُ اللَّهُ بما آتَاهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1054]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1054]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ጌታው የተመራና ለእስልምና የተገጠመ፤ ምንም ሳይጨመርና ሳይቀነስ የሚበቃውን ያህል ሐላል ሲሳይ የተለገሰና አላህ በሰጠው ነገር እንዲወድና እንዲብቃቃ የተደረገ ሰው በርግጥም ስኬታማና እድለኛ መሆኑን ገለፁ።