+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قالَ: قالَ رَسُولُ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ عليْه وسلَّمَ:
«دِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ فِي سَبِيلِ اللهِ، وَدِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ فِي رَقَبَةٍ، وَدِينَارٌ تَصَدَّقْتَ بِهِ عَلَى مِسْكِينٍ، وَدِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ عَلَى أَهْلِكَ أَعْظَمُهَا أَجْرًا الَّذِي أَنْفَقْتَهُ عَلَى أَهْلِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 995]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"በአላህ መንገድ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ባሪያ ነፃ ለማውጣት ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለሚስኪን ምፅዋት ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለቤተሰቦችህ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር መካከል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ለቤተሰብህ ወጪ ያደረግከው ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 995]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንዳንድ የምፅዋት አይነቶችን እንዲህ በማለት አወሱ። "በአላህ መንገድ ለሚደረግ ትግል ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ ከባርነት ነፃ ለማውጣት ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ የሚያስፈልገው ለሆነ ሚስኪን ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር፣ ለቤተሰብህና ለዘመዶችህ ወጪ ያደረግከው አንድ ዲናር ይኖራል።" ቀጥለውም ከነዚህ መካከል አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ዲናር ቀለብ ግዴታ ለሆነብህ የቤተሰብ አካል የምታወጣው ወጪ እንደሆነ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ መንገድ ወጪ የማድረጊያ መንገዶች ብዙ እንደሆኑ እንረዳለን።
  2. ወጪ የምናደርግባቸው መንገዶች በዝተው በሚያጨናንቁን ጊዜ በላጩን ማስቀደም ይገባል። ከነዚህም መካከል አንዱ ሁሉንም ማድረግ በማይቻልበት ወቅት ለቤተሰብ ወጪ ማድረግ ነው።
  3. ነወዊይ በሙስሊም ማብራሪያቸው እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለቤተሰብ ወጪ በማድረግ ላይ የሚያነሳሳ ነው። ለቤተሰብ በሚወጣ ወጪ የሚገኘው ምንዳም ትልቅ መሆኑን ይገልፃል። ምክንያቱም ከቤተሰብ መካከል በቅርበቱ ምክንያት ቀለብ ግዴታ የሚሆንብን አካል አለ። ከቤተሰብ መካከል ለርሱ ወጪ ማድረጋችን የሚወደድልን አለ። በዛውም ዝምድናን መቀጠልና ምፅዋት ይሆንልናል። ከቤተሰብ መካከል በጋብቻ ወይም በባርነት የራሳችን ስላደረግናቸው ለነርሱ ወጪ ልናደርግላቸው ግዴታ የሆኑብንም አሉ። ይህ ሁሉ በላጭና የተበረታታ ተግባር ነው። ይህም ከትርፍ ምፅዋቶች ሁሉ በላጩ ነው።"
  4. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ለቤተሰቡ ወጪ ያደረገው አንድ ዲናር) ማለታቸው የአላህን ፊት ፈልጎ ያደረገ ጊዜ ነው። ለምሳሌ የቤተሰብን ሐቅ መወጣት ፈልጎ ያደረገ ጊዜ ማለት ነው።"
  5. አቡ ቂላባህ እንዲህ ብለዋል: "ለትናንሽ የቤተሰቡ አባላት ውጪ አድርጎ እነርሱን ከሰው እጅ ከሚጠብቃቸው ወይም አላህ በርሱ ሰበብ ቤተሰቡን ከሌሎች የሚያብቃቃበት ከሆነ ሰውዬ የበለጠ ትልቅ ምንዳ ያለው ማን አለና?!"
ተጨማሪ