عَنْ إِيَاسِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي ذُبَابٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَضْرِبُوا إِمَاءَ اللَّهِ» فَجَاءَ عُمَرُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: ذَئِرْنَ النِّسَاءُ عَلَى أَزْوَاجِهِنَّ، فَرَخَّصَ فِي ضَرْبِهِنَّ، فَأَطَافَ بِآلِ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نِسَاءٌ كَثِيرٌ يَشْكُونَ أَزْوَاجَهُنَّ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَقَدْ طَافَ بِآلِ مُحَمَّدٍ نِسَاءٌ كَثِيرٌ يَشْكُونَ أَزْوَاجَهُنَّ، لَيْسَ أُولَئِكَ بِخِيَارِكُمْ».
[صحيح] - [رواه أبو داود وابن ماجه] - [سنن أبي داود: 2146]
المزيــد ...
ከኢያስ ቢን ዐብደላህ ቢን አቢ ዙባብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ:
"የአላህን ሴት ባሮች አትምቱ!" ዑመርም ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት እንዲህ አሏቸው: "ሴቶች በባሎቻቸው ላይ እያመፁ ነው።" የዛኔም እንዲመቷቸው ፈቀዱ። የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታቸውን አሰሙ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በሙሐመድ ሚስቶች ዙሪያ በርካታ ሴቶች ስለባሎቻቸው ቅሬታ አሰምተዋል። እነዚህ ሚስቶቻቸውን የሚመቱ ባሎች ምርጦች አይደሉም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 2146]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶችን ከመምታት ከለከሉ። የአማኞች አዛዥ ዑመር ቢን አልኸጧብም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሴቶች ባሎቻቸውን ተዳፈሩ። ስነምግባራቸውም ተበላሸ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የባልን ሐቅ አለመወጣት እምቢተኝነትን ማሳየት፣ ባልን ማመፅና የመሳሰሉት ምክንያቶች ከተከሰቱ የማያቆስል ምት እንዲመቷቸው ፈቀዱ። ከዛም በኋላ ባሎቻቸው ይህንን ፍቃድ በመጥፎ መንገድ በመጠቀም የሚያቆስል ምት የመቷቸው ሚስቶች የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሚስቶች ዘንድ ቅሬታ ሊያሰሙ መጡ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: ከናንተ ምርጦቹ እነዚያ ሚስቶቻቸውን የሚያቆስል ምት የሚማቱት ወንዶች አይደሉም።