عن أسامة بن زيد رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَا تَرَكْتُ بَعْدِي فِتْنَةً أَضَرَّ عَلَى الرِّجَالِ مِنَ النِّسَاءِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5096]
المزيــد ...
ከኡሳማህ ቢን ዘይድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5096]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሳቸው በኋላ በወንዶች ላይ ከሴቶች የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተናና መሞከሪያ እንዳልተዉ ተናገሩ። ወንዶች በሴቶች መጎዳታቸው ሴቷ ከቤተሰቡ አባላት ከሆነች ሸሪዓን በሚፃረር ጉዳይ እሷን በመከተል ይከሰታል። ባዳ ከሆነች ደግሞ ከሷ ጋር በመቀላቀልና ለብቻቸው በመገለል በርሱ ሳቢያ ብልሽቶችን የሚያመጡ ነገሮችን በመፈፀም ነው።