عَنْ ابْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهُما أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا حَقُّ امْرِئٍ مُسْلِمٍ لَهُ شَيْءٌ يُوصِي فِيهِ، يَبِيتُ ثَلَاثَ لَيَالٍ، إِلَّا وَوَصِيَّتُهُ عِنْدَهُ مَكْتُوبَةٌ»، قَالَ عَبْدُ اللهِ بْنُ عُمَرَ رضي الله عنهما: «مَا مَرَّتْ عَلَيَّ لَيْلَةٌ مُنْذُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ ذَلِكَ إِلَّا وَعِنْدِي وَصِيَّتِي».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1627]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰማ:
"ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።" ዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አላደርኩም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1627]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም የሆነ ሰው ትንሽ ብትሆን እንኳ አንዳች የሚናዘዘው ሐቅ ወይም ገንዘብ ኖሮ ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናትን ማደር እንደማይገባው ተናገሩ። ዐብደላህ ቢን ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: " የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አድሬ አላውቅም።"