عَن سَهْلِ بْنِ حُنَيْفٍ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ سَأَلَ اللهَ الشَّهَادَةَ بِصِدْقٍ بَلَّغَهُ اللهُ مَنَازِلَ الشُّهَدَاءِ، وَإِنْ مَاتَ عَلَى فِرَاشِهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1909]
المزيــد ...
ከሰህል ቢን ሑነይፍ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1909]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ሰማእት መሆንንና መገደልን የፈለገ፣ በዚህ ፍላጎቱም ለአላህ አጥርቶና እውነተኛ ሆኖ ከሆነ የጠየቀው ጂሀድ ሳያደርግ ፍራሽ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ በእውነተኛ ኒያው የሰማእታትን ደረጃ እንደሚሰጠው ተናገሩ።