عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا يَزَالُ البَلاَءُ بِالمُؤْمِنِ وَالمُؤْمِنَةِ فِي نَفْسِهِ وَوَلَدِهِ وَمَالِهِ حَتَّى يَلْقَى اللَّهَ وَمَا عَلَيْهِ خَطِيئَةٌ».
[حسن] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 2399]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
"አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»
[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2399]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ የሆነ ወንድና ሴት ባሪያ ከፈፀማቸው ሁሉም ወንጀሎችና ኃጢዐቶች የፀዳ ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስና በነዚህ መከራዎች ሁሉንም ወንጀሎቹን አላህ እስኪምረው ድረስ በነፍሱ (በጤናውና በአካሉ)፣ በልጆቹ (በህመም ወይም ሞት ወይም በነርሱ በመበደል ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ በልጆች ሳቢያ በሚደርሱ መከራዎች)፣ በገንዘቡ (በመደኽየት፣ ንግዱን በመክሰር፣ በመሰረቅ፣ በኑሮ መወደድ፣ በሲሳይ መጥበብ) የሚያጋጥመው መከራና ፈተና አይላቀቀውም።