عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضيَ اللهُ عنهما:
أنَّهُ قَالَ لعَطَاءِ بْنِ أَبِي رَبَاحٍ: أَلَا أُرِيكَ امْرَأَةً مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ؟ قُلْتُ: بَلَى، قَالَ: هَذِهِ الْمَرْأَةُ السَّوْدَاءُ، أَتَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَتْ: إِنِّي أُصْرَعُ وَإِنِّي أَتَكَشَّفُ، فَادْعُ اللهَ لِي، قَالَ: «إِنْ شِئْتِ صَبَرْتِ وَلَكِ الْجَنَّةُ، وَإِنْ شِئْتِ دَعَوْتُ اللهَ أَنْ يُعَافِيَكِ» قَالَتْ: أَصْبِرُ، قَالَتْ: فَإِنِّي أَتَكَشَّفُ فَادْعُ اللهَ أَنْ لَا أَتَكَشَّفَ، فَدَعَا لَهَا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2576]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2576]
ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለዐጧእ ቢን አቢረባሕ እንዲህ አሉ: "የጀነት ነዋሪ የሆነችን ሴት አላሳይህምን?" ዐጧእም "እንዴታ!" አለ። ኢብኑ ዐባስም እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሐበሻዊት ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: "የሚጥል በሽታ ስላለብኝ ይጥለኝና እገላለጣለሁኝ። ታዲያ እኔ ሳላውቀው ከሰውነቴ የተወሰነው ክፍል ይገለጣል። አላህ ጤናን እንዲለግሰኝ ለምኑልኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ጤናን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁኝ።" እርሷም እንዲህ አለች: "እንዲህ ከሆነ እታገሳለሁኝ። አክላም "ስወድቅ እንዳልገላለጥ ግን አላህን ይለምኑልኝ።" አለች። እርሳቸውም አላህን ለመኑላት።