عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا انْتَهَى أَحَدُكُمْ إِلَى الْمَجْلِسِ فَلْيُسَلِّمْ، فَإِذَا أَرَادَ أَنْ يَقُومَ فَلْيُسَلِّمْ، فَلَيْسَتِ الْأُولَى بِأَحَقَّ مِنَ الْآخِرَةِ».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 5208]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡
"አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።"
[ሐሰን ነው።] - [An-Nasaa’i] - [ሱነን አቡዳውድ - 5208]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰዎች ወደ ተቀማመጡበት ስፍራ የመጣ ሰው ሰላምታ እንዲያቀርብና መነሳትም የፈለገ ጊዜ የተቀማመጡትን ሰዎች በድጋሚ ሰላምታ እንዲያቀርብላቸው ጠቆሙ። በሚመጣበት ወቅት (ሲቀላቀላቸው) ያቀረበው የመጀመሪያው ሰላምታ በሚለያይበት ወቅት (ሲሰናበታቸው) ከሚያቀርበው የመጨረሻ ሰላምታ የበለጠ የሚያደርገው ነገር እንደሌለ ተናገሩ።