+ -

عَنْ مَطَرِ بْنِ عُكَامِسٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا قَضَى اللَّهُ لِعَبْدٍ أَنْ يَمُوتَ بِأَرْضٍ جَعَلَ لَهُ إِلَيْهَا حَاجَةً».

[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2146]
المزيــد ...

መጠር ቢን ዑካሚስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2146]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ አንድ ባሪያ እሱ በማይኖርበት አንድ ስፍራ እንዲሞት አላህ የወሰነና የፈረደ ጊዜ ወደዛ ስፍራ የሚሄድበት ምክንያት (ጉዳይ) ያደርግበትና ይሄዳል። እዛም ስፍራ ላይ ነፍሱ ትያዛለች። በማለት ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ {ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም።} ለሚለው የአላህ ንግግር ማረጋገጫ ነው።