+ -

عَنْ طَاوُسٍ أَنَّهُ قَالَ: أَدْرَكْتُ نَاسًا مِنْ أَصْحَابِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، يَقُولُونَ كُلُّ شَيْءٍ بِقَدَرٍ، قَالَ: وَسَمِعْتُ عَبْدَ اللهِ بْنَ عُمَرَ رضي الله عنهما يَقُولُ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«كُلُّ شَيْءٍ بِقَدَرٍ، حَتَّى الْعَجْزِ وَالْكَيْسِ، أَوِ الْكَيْسِ وَالْعَجْزِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2655]
المزيــد ...

ጣዉስ እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች የሆኑ ሰዎችን አግኝቻለሁ። "ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ ነው"ይሉም ነበር። ጣዉስ እንዲህም አሉ፦ " ዐብደላህ ቢን ዑመርን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2655]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ መሆኑን ገለፁ። ስንፍና ሳይቀር ተወስኗል: እሱም: - ዱንያዊና አኺራዊ ከሆኑ ጉዳዮች መስራት ግድ የሆነበትን ነገር መተው፣ ሳይሰሩ መገኘት ፣ ከወቅቱ ማዘግየት ነው። ጮሌነት ሳይቀር ተወስኗል: እሱም:- ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳዮችን ለመስራት መነቃቃትና ብልህ መሆን ማለት ነው። የላቀውና የተከበረው አላህ ስንፍናና ጮሌነትን ሳይቀር ሁሉንም ነገር ወስኗል። በዚህ ዓለም የአላህ ዕውቀትና ፍላጎት የቀደመው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አይከሰትም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ ውሳኔ (ቀደር) ጉዳይ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እምነት መገለፁ።
  2. ስንፍናና ንቁነት ሳይቀር ሁሉም ነገር የሚከሰተው በአላህ ውሳኔ መሆኑን፤
  3. የአላህ መልክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐዲሥ በማስተላለፉ ረገድ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ጥንቃቄና ማረጋገጥ፤
  4. በመልካሙም ሆነ በመጥፎው ሁሉም ጉዳይ በአላህ ውሳኔ መሆኑን ማመንን ተረድተናል።
ተጨማሪ