عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنهما قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«كَتَبَ اللهُ مَقَادِيرَ الْخَلَائِقِ قَبْلَ أَنْ يَخْلُقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِخَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ، قَالَ: وَعَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2653]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዐስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል።" እንዲህም አሉ፦ " ዐርሹ ውኃ ላይ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2653]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በፍጡራኖች ላይ የሚከሰተውን ውሳኔዎች ህይወት፣ ሞት፣ ሲሳይና ሌሎችንም ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት በዝርዝር በጥብቅ ሰሌዳ ውስጥ እንደፃፈውና እሱም አላህ በወሰነው መልኩ የሚከሰት መሆኑን ተናገሩ። ሁሉም የሚከሰቱ ነገሮች በአላህ ፍርድና ውሳኔ መሰረት ነው። አንድ ሰውን ያገኘው ነገር ቀድሞውኑ ሊስተው አይችልም ነበር፤ የሳተውም ነገር ሊያገኘው አይችልም ነበር።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ ፍርድና ቅድመ ውሳኔ ማመን ግዴታ መሆኑን እንረዳለም።
  2. ቀደር (ውሳኔ) ሲባል :- አላህ በነገሮች ላይ ያለውን ዕውቀት፣ መፃፉን፣ መሻቱንና መፍጠሩን የሚያጠቃልል ነው።
  3. ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ውሳኔዎች እንደተፃፉ ማመን በሚያጋጥሙን ነገሮች መውደድና መቀበልን ይፈይደናል።
  4. ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የአርረሕማን ዐርሽ ውኃ ላይ ነበር።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (65)
ተጨማሪ