+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
حَدَّثَنَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَهُوَ الصَّادِقُ المَصْدُوقُ: «أَنَّ خَلْقَ أَحَدِكُمْ يُجْمَعُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا وَأَرْبَعِينَ لَيْلَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَهُ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَهُ، ثُمَّ يُبْعَثُ إِلَيْهِ المَلَكُ، فَيُؤْذَنُ بِأَرْبَعِ كَلِمَاتٍ، فَيَكْتُبُ: رِزْقَهُ وَأَجَلَهُ وَعَمَلَهُ وَشَقِيٌّ أَمْ سَعِيدٌ، ثُمَّ يَنْفُخُ فِيهِ الرُّوحَ، فَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ الجَنَّةِ حَتَّى لاَ يَكُونُ بَيْنَهَا وَبَيْنَهُ إِلَّا ذِرَاعٌ، فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الكِتَابُ، فَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ فَيَدْخُلُ النَّارَ، وَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَيَعْمَلُ بِعَمَلِ أَهْلِ النَّارِ حَتَّى مَا يَكُونُ بَيْنَهَا وَبَيْنَهُ إِلَّا ذِرَاعٌ، فَيَسْبِقُ عَلَيْهِ الكِتَابُ، فَيَعْمَلُ عَمَلَ أَهْلِ الجَنَّةِ فَيَدْخُلُهَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7454]
المزيــد ...

ዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ:
እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጻፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የእሳት ጉዶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7454]

ትንታኔ

ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አለ፦ በንግግራቸው እውነተኛ የሆኑትና አላህ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጡ እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ነገሩን: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ፍጥረቱ ይሰበሰባል" ይህም አንድ ወንድ ባለቤቱን የተገናኘ ጊዜ የተበታተነው ዘር ፈሳሹ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ለአርባ ቀን የዘር ፈሳሽ ሆኖ ይሰበሰባል። ከዚያም የረጋ ደም ይሆናል። ይህም የደረቀ ወፍራም ደም ነው። ይህ በሁለተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ቁራጭ ስጋ ይሆናል። ይህም የሚታኘክ የሚያህል ቁራጭ ስጋ ነው። ይህ በሶስተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ወደርሱ አላህ መልዐክ ይልካል። ሶስተኛው አርባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፅንሱ ውስጥ ሩሕ (ነፍስ) ይነፋበታል። መልዐኩ አራት ን መልእክቶችን እንዲጽፍ ይታዘዛል። እነሱም:- ሲሳዩን: ይህም በእድሜው ውስጥ ምን ያህል መጠን ነው የሚያገኘው ፀጋ የሚለውን ነው። የሞት ቀጠሮውን:- ይህም በዱንያ ውስጥ የሚቆይበትን ዘመን ነው። ሥራውን:- ምንድነው እሱ? እድለቢስ ነው ወይስ እድለኛ? ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ማሉ። አንዱ የጀነት ሰዎችን ሥራ ይሠራል፤ ሥራው ለሰዎች በሚታየው መልካም ይሆናል፤ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል እስኪቀር በዚው መልክ ይቀጥላል። ማለትም አንድ ያሰበው ቦታ ለመድረስ አንድ ክንድ እንደቀረው ሰው በርሱና ጀነት በመግባት መካከልም አንድ ክንድ በስተቀር ምንም አይቀርም። በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና በዛን ወቅት የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና በዛው ላይ ፍፃሜው ይሆናል። እሳትም ይገባል። ሥራ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ መስፈርት በዛው ላይ መፅናትና አለመለወጥ ነውና። ከሰዎች ሌላኛው ደግሞ እሳት ለመግባት እስኪቀርብ ድረስ የእሳት ባለቤቶችን ሥራ ይሠራል፤ በርሱና በእሳት መካከል የምድር አንድ ክንድ ያህል የቀረው እስኪመስል ድረስ፤ በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነገሮች ፍፃሜ መዳረሻቸው በቀደመው ውሳኔና በተፃፈው ፍርድ መሰረት ነው።
  2. ሥራዎች የሚለኩት በፍፃሜያቸው ስለሆነ በሥራዎች ይዘት ከመሸወድ ማስጠንቀቅን ተረድተናል።