+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«نَارُكُمْ جُزْءٌ مِنْ سَبْعِينَ جُزْءًا مِنْ نَارِ جَهَنَّمَ»، قِيلَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنْ كَانَتْ لَكَافِيَةً. قَالَ: «فُضِّلَتْ عَلَيْهِنَّ بِتِسْعَةٍ وَسِتِّينَ جُزْءًا كُلُّهُنَّ مِثْلُ حَرِّهَا».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3265]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነት (አቃጣይነት) ነው ያላቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3265]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የዱንያ እሳት ከሰባ የጀሀነም እሳት ክፍል አንዷ ክፍል መሆኗን ተናገሩ። የአኺራ እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ እጥፍ የማቃጠል ደረጃዋ ይበልጣል። እያንዳንዱ የጀሀነም ክፍል ከዱንያ እሳት አቃጣይነት ጋር እኩል ነው። "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀሀነም ውስጥ የሚገቡን ለመቅጣት የዱንያ እሳት’እኮ በቂ ነበረች።" ተባሉ። እርሳቸውም "የጀሀነም እሳት ከዱንያ እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጓል። የእያንዳንዱ ክፍል ሀሩርነት (የማቃጠል) ኃይልም እንደ ዱንያ እሳት አምሳያ ነው።" አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰዎች ወደ እሳት ከሚያደርሱ ሥራዎች እንዲርቁ ከእሳት ማስጠንቀቅ፤
  2. የጀሀነም እሳት ትልቅነቷ፣ ቅጣቷና የሀሩርነቷን ኃይለኝነት ተረድተናል።
ተጨማሪ