+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يُؤْتَى بِالْمَوْتِ كَهَيْئَةِ كَبْشٍ أَمْلَحَ، فَيُنَادِي مُنَادٍ: يَا أَهْلَ الجَنَّةِ، فَيَشْرَئِبُّونَ وَيَنْظُرُونَ، فَيَقُولُ: هَلْ تَعْرِفُونَ هَذَا؟ فَيَقُولُونَ: نَعَمْ، هَذَا المَوْتُ، وَكُلُّهُمْ قَدْ رَآهُ، ثُمَّ يُنَادِي: يَا أَهْلَ النَّارِ، فَيَشْرَئِبُّونَ وَيَنْظُرُونَ، فَيَقُولُ: وهَلْ تَعْرِفُونَ هَذَا؟ فَيَقُولُونَ: نَعَمْ، هَذَا المَوْتُ، وَكُلُّهُمْ قَدْ رَآهُ، فَيُذْبَحُ ثُمَّ يَقُولُ: يَا أَهْلَ الجَنَّةِ خُلُودٌ فَلاَ مَوْتَ، وَيَا أَهْلَ النَّارِ خُلُودٌ فَلاَ مَوْتَ، ثُمَّ قَرَأَ: {وَأَنْذِرْهُمْ يَوْمَ الحَسْرَةِ إِذْ قُضِيَ الأَمْرُ وَهُمْ فِي غَفْلَةٍ} [مريم: 39]، وَهَؤُلاَءِ فِي غَفْلَةٍ أَهْلُ الدُّنْيَا {وَهُمْ لاَ يُؤْمِنُونَ} [مريم: 39]».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4730]
المزيــد ...

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት ይጣራል "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ይታረዳል ቀጥሎ እንዲህ ይላቸዋል "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የሚለውን አንቀፅ አነበቡ። "እነዚህ በዱንያ ዝንጋቴ ውስጥ ናቸው።" {እነሱም የማያምኑ ናቸው።} [መርየም: 39]"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4730]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን ሞት ጥቁርና ነጭ በሆነ ወንድ በግ ተመስሎ ተይዞ እንደሚመጣ አብራሩ። "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተብሎ ይጠራል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል ያውቀዋል።" ይላሉ። ከዚያም ተጣሪው "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" በማለት ይለፍፋል። አንገቶቻቸውንና ትከሻዎቻቸውን በመለጠጥ ጭንቅላታቸውንም በማንጠራራት ይመለከታሉ። ለነሱም "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። እነሱም "አዎን ይህ ሞት ነው። ሁሉም አይቶታል።" ይላሉ። ሙክቱ ይታረዳል ከዚያም ተጣሪው፦ "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! እጣፈንታችሁ ያለሞት ዘውትርና ዘላለም መኖር ነው።" ይላቸዋል። ይህም ለአማኞች ተጨማሪ ፀጋ ለከሀዲያን የቅጣት አለንጋ እንዲሆን ነው። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህን አንቀፅ አነበቡ። {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ እነሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የትንሳኤ ቀን በጀነትና እሳት ባለቤቶች መሀል ይፈረዳል። ሁሉም ወደሚዘወትርባት ይገባል። ወንጀለኛ በጎ ባለመሥራቱ ይፀፀታልም ይቆጫልም። መልካም ከመስራት ያጓደለም ባለመጨመሩ ይቆጫል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ በመጪው ዓለም መመለሻው ጀነት ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ መዘውተር ነው።
  2. ስለ ትንሳኤ ቀን መከራ ከባድ ማስፈራሪያ መምጣቱ። እሱ የቁጭትና ፀፀት ቀን ነው።
  3. የጀነት ባለቤቶች ደስታ እንደሚዘወትር፤ የእሳት ባለቤቶች ሀዘንም እንደሚዘወትር መገለፁ።
ተጨማሪ