عن ابن عباس رضي الله عنهما قال:
كُنْتُ خَلْفَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَوْمًا، فَقَالَ: «يَا غُلَامُ، إِنِّي أُعَلِّمُكَ كَلِمَاتٍ، احْفَظِ اللهَ يَحْفَظْكَ، احْفَظِ اللهَ تَجِدْهُ تُجَاهَكَ، إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللهِ، وَاعْلَمْ أَنَّ الْأُمَّةَ لَوِ اجْتَمَعَتْ عَلَى أَنْ يَنْفَعُوكَ بِشَيْءٍ، لَمْ يَنْفَعُوكَ إِلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ لَكَ، وَلَوِ اجْتَمَعُوا عَلَى أَنْ يَضُرُّوكَ بِشَيْءٍ، لَمْ يَضُرُّوكَ إِلَّا بِشَيْءٍ قَدْ كَتَبَهُ اللهُ عَلَيْكَ، رُفِعَتِ الْأَقْلَامُ وَجَفَّتِ الصُّحُفُ».

[صحيح] - [رواه الترمذي]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
አንድ እለት ከአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኋላ ሳለሁ እንዲህ አሉኝ "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ ፅፎብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ጽሑፉም ደርቋል።"

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እየጋለበ ሳለ ለሱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል : እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አሳውቅሀለሁ።
አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎች የአላህ ጥበቃና ወደየትም ብትዞር የቸገረህን በመርዳት አላህም የሚጠብቅህ ይሆናል።
አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! የጠያቂዎችን ልመና የሚቀበለው እሱ ብቻ ነውና።
እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ!
የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አለህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማይደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር!
ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ህፃናትና ትናንሽ ልጆችን እንደ ተውሒድ፣ አዳቦችና ሌሎችንም የዲን ጉዳዮችን የማስተማር አንገብጋቢነት ፤
  2. ምንዳ በስራው አይነት እንደሆነ ፤
  3. ከሱ ውጪ ያለን ሁሉ በመተው በአላህ ላይ ብቻ መደገፍና በሱ ላይ ብቻ መመካት መታዘዙን ፤ እሱስ ምንኛ ያማረ መመኪያ ነው!
  4. በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመንና በፍርዱ መውደድ እንዳለብን ፤ አላህ ሁሉንም ነገር ወስኗልና።
  5. የአላህን መመርያ የጣሰ ሰው አላህ ያጠፋዋል እንጂ እንደማይጠብቀው ተምረናል።
ተጨማሪ