عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: بَلَغَ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ أَصْحَابِهِ شَيْءٌ، فَخَطَبَ فَقَالَ:
«عُرِضَتْ عَلَيَّ الْجَنَّةُ وَالنَّارُ فَلَمْ أَرَ كَالْيَوْمِ فِي الْخَيْرِ وَالشَّرِّ، وَلَوْ تَعْلَمُونَ مَا أَعْلَمُ لَضَحِكْتُمْ قَلِيلًا وَلَبَكَيْتُمْ كَثِيرًا» قَالَ: فَمَا أَتَى عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم يَوْمٌ أَشَدُّ مِنْهُ، قَالَ: غَطَّوْا رُءُوسَهُمْ وَلَهُمْ خَنِينٌ، قَالَ: فَقَامَ عُمَرُ فَقَالَ: رَضِينَا بِاللهِ رَبًّا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا، وَبِمُحَمَّدٍ نَبِيًّا، قَالَ: فَقَامَ ذَاكَ الرَّجُلُ فَقَالَ: مَنْ أَبِي؟ قَالَ: «أَبُوكَ فُلَانٌ»، فَنَزَلَتْ: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لا تَسْأَلُوا عَنْ أَشْيَاءَ إِنْ تُبْدَ لَكُمْ تَسُؤْكُمْ} [المائدة: 101].
المزيد
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከባልደረቦቻቸው አንድ ጉዳይ ደረሳቸውና ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ:
"በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።"» አነስ እንዲህ አለ: "በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶሓቦች ላይ ከዚህ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን መጥቶ አያውቅም።" አነስ እንዲህም አለ: «ሶሓቦች ጭንቅላታቸውን ሸፍነው እየተንሰቀሰቁ አለቀሱ። ዑመርም ተነሳና እንዲህ አለ: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት ወደድን።" ያ ሰውዬም ተነሳና እንዲህ አለ: "አባቴ ማን ነው?" እርሳቸውም "አባትህ እገሌ ነው።" አሉት። በዚህም ጊዜ ይህቺ አንቀፅ ወረደች {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለፁ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ።} [አልማኢዳህ:101]»