عَنْ المِقْدَادِ بْنَ عَمْرٍو الكِنْدِيَّ رضي الله عنه:
أَنَّهُ قَالَ لِرَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَرَأَيْتَ إِنْ لَقِيتُ رَجُلًا مِنَ الكُفَّارِ فَاقْتَتَلْنَا، فَضَرَبَ إِحْدَى يَدَيَّ بِالسَّيْفِ فَقَطَعَهَا، ثُمَّ لاَذَ مِنِّي بِشَجَرَةٍ، فَقَالَ: أَسْلَمْتُ لِلَّهِ، أَأَقْتُلُهُ يَا رَسُولَ اللَّهِ بَعْدَ أَنْ قَالَهَا؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لاَ تَقْتُلْهُ» فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّهُ قَطَعَ إِحْدَى يَدَيَّ، ثُمَّ قَالَ ذَلِكَ بَعْدَ مَا قَطَعَهَا؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لاَ تَقْتُلْهُ، فَإِنْ قَتَلْتَهُ فَإِنَّهُ بِمَنْزِلَتِكَ قَبْلَ أَنْ تَقْتُلَهُ، وَإِنَّكَ بِمَنْزِلَتِهِ قَبْلَ أَنْ يَقُولَ كَلِمَتَهُ الَّتِي قَالَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4019]
المزيــد ...
ከሚቅዳድ ቢን ዐምር አልኪንዲይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
እርሱ ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አላቸው: «ከከሀዲዎች መካከል ከአንዱ ጋር ብንገናኝና ብንጋደል አንድ እጄንም በሰይፉ መቶ ቢቆርጣት ከዚያም ከኔ ለማምለጥ ወደ ዛፍ ተጠግቶ ለአላህ ብዬ እስልምናን ተቀብያለሁ ቢል የአላህ መልክተኛ ሆይ! ንገሩኝ እስኪ ይህን ከተናገረ በኋላ ልግደለውን? የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው።" አሉ። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ እጄን‘ኮ ቆርጧል። ከዚያም እጄን ከቆረጣት በኋላ ነው ይህቺን የተናገራት!" አለ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው! ከገደልከው እርሱ ከመግደልህ በፊት የነበርክበት ደረጃ ላይ ይሆንና አንተ ደሞ የተናገረውን ንግግር ከመናገሩ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ ትሆናለህ።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4019]
ሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና -ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጦርነት ላይ ከአንድ ከሀዲ ሰው ጋር ቢገናኝና በሰይፍ ብቻ ለብቻ ቢጋጠሙ ከሀዲውም አንድ እጁን በሰይፍ አግኝቶ ከቆረጠ በኃላ ከርሱ ሸሽቶ በዛፍ ቢመሸግና "ላኢላሃ ኢለሏህ" ቢል እጄን ከቆረጠ በኋላ እርሱን መግደል ይፈቀድልኛልን? በማለት ጠየቀ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳትገድለው! አሉት።
እርሱም: የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሱ’ኮ አንድ እጄን ቆርጧል። ይህን ከማድረጉም ጋር አልገድለውምን? አላቸው።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እንዳትገድለው! እርሱ ደሙን ማፍሰስ ከተከለከሉት ሆኗል። ከሰለመ በኋላ ከገደልከው እርሱ በእስልምናው ደሙ የተጠበቀ ስለሆነ ባንተ ደረጃ ይሆንና አንተ ደሞ እርሱን በመግደልህ በቂሷስ ህግ መሰረት ደምህ መፍሰሱ የተፈቀደ ስለምትሆን በርሱ ደረጃ ላይ ትሆናለህ! አሉት።