عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَحْسَنَ النَّاسِ خُلُقًا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2310]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2310]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ሁሉ ስነምግባራቸው እጅግ የተሟላ ሰው ናቸው። ንግግርን በማሳመር፣ መልካምን በመለገስ፣ ፊታቸው በመፍታት፣ መጥፎ ከመስራት በመቆጠብ፣ ሌሎች የሚያደርሱባቸውን ጉዳት በመቻል በሁሉም ስነምግባሮችና መልካምነት ባጠቃላይ ግንባር ቀደም ናቸው።