+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ، وَكَانَ يَلْقَاهُ فِي كُلِّ لَيْلَةٍ مِنْ رَمَضَانَ فَيُدَارِسُهُ القُرْآنَ، فَلَرَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدُ بِالخَيْرِ مِنَ الرِّيحِ المُرْسَلَةِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር። በረመዷን ውስጥም በየሁሉም ምሽት ያገኛቸውና ቁርአን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ንፋስም የበለጠ በመልካም ነገር ላይ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው:
የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤
ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው።
ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቸርነት፣ የደግነታቸው ስፋት መገለፁ። በተለይ በረመዷን ወር። ይህም ወሩ የአምልኮ ወርና የመልካም መሸመቻ ወር ስለሆነ ነው።
  2. በሁሉም ወቅት ቸር በመሆን ላይ መነሳሳቱንና በረመዷን ወር ደግሞ ቸርነትን መጨመር እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. በረመዷን ወር አብዝቶ መለገስ፣ መስጠት፣ በጎ መስራትና ቁርአን መቅራት እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. እውቀትን ለመሸምደድ ከሚረዱ ሰበቦች አንዱ ከእውቀት ፈላጊዎችና ዑለሞች ጋር መማማሩ ነው።