عَنْ حُذَيْفَةَ بْنِ اليَمَانِ رَضيَ اللهُ عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ إِذَا أَرَادَ أَنْ يَنَامَ وَضَعَ يَدَهُ تَحْتَ رَأْسِهِ، ثُمَّ قَالَ: «اللَّهُمَّ قِنِي عَذَابَكَ يَوْمَ تَجْمَعُ أَوْ تَبْعَثُ عِبَادَكَ».
[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3398]
المزيــد ...
ሑዘይፋህ ቢን አል'የማን -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዳስተላለፉት:
«ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መተኛት የፈለጉ ጊዜ እጃቸውን ጭንቅላታቸው ስር ያኖሩ ነበር። ቀጥለውም እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል። - An-Nasaa’i - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3398]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመተኛት ስፍራቸውን ሲይዙ ቀኝ እጃቸውን ይንተራሱና ቀኝ ጉንጫቸውን ቀኝ እጃቸው ላይ በማኖር እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበክ" አላህ ሆይ! ጌታዬ ቅጣትህን ጠብቀኝ። "የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ" የሒሳብ ቀን የትንሳኤ ቀን ማለት ነው።